Skip to main content
zena63

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ተሳትፎና በራስ አቅም የተገነባ የህብረት ተምሳሌት ነው (መስከረም 5/2017) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር ተቋማት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ምረቃን አስመልክቶ "እመርታና ማንሠራራት" በሚል ሀሳብ ፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የፓናል ውይይት መድረኩን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ተሳትፎና በራስ አቅም የተገነባ፣ የህብረት ተምሳሌት ነው። ግድቡ የይቻላልን በተግባር ማሳየት የተቻለበት ታላቁ የክፍለ-ዘመን ጀግንነት የታየበት ነው፤ የጋራ ማህተም ያረፈበት የኢትዮጵያውያን ስጦታም ጭምር ነው ሲሉ አቶ ሳሙኤል አክለው ገልጸዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባሳለፍነው ጷጉሜ 04 በይፋ መመረቁ ይታወሳል።