በጉራጌ ዞን የሚገኙ ወጣቶች በአዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራ ላይ የተሻለ ክህሎት እንዳላቸውና ይህንን ወደ ውጤት በመቀየር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላቶች በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ። ጉራጌ ዞን የሳይንስ ፣የኢኖቬሽን እና የቴክኖሎጂ ማዕከል እናድርግ በሚል የዞኑ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 በጀት እቅድ ከባለ ድርሻ አካላት…
የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ አስመልክቶ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። ወራቤ፣ መስከረም 8/2018 (ስልጤ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን) ከስልጤ ዞን የተለያዩ አከባቢዎች የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበትና በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ምረቃ በማስመልከት የተዘጋጀ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። ህዝባዊ ሰልፉ ኢትዮጵያዊያን ከትልቅ እስከ ትንሽ ሀብታም ደሃ…
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ተሳትፎና በራስ አቅም የተገነባ የህብረት ተምሳሌት ነው (መስከረም 5/2017) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር ተቋማት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ምረቃን አስመልክቶ "እመርታና ማንሠራራት" በሚል ሀሳብ ፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የፓናል ውይይት መድረኩን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ተሳትፎና በራስ አቅም…
የሳይበር ጥቃት መከላከል ወትሮ ዝግጁነት በማረጋገጥ ረገድ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ። ስኬታማ እና ዘላቂ የሳይበር መከላከል ወትሮ ዝግጁነት በማረጋገጥ ረገድ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ሀገራዊ የሳይበር ጥቃት መከላከል ወትሮ ዝግጁነት ላይ ያተኮረ ውይይት ከተለያዩ ባለድሻ አካላት ጋር (የጸጥታና ደህንነት ተቋማት፣ ቁልፍ መሰረተ ልማት የሚያስተዳድሩ ተቋማት፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ ሚዲያ ወ.ዘ.ተ)…
የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች አጠቃቀምንና አቅርቦትን በማሳደግ ከወረቀት ነጻ የሆኑ አገልግሎቶችን መስጠት ላይ የተጀመረውን ስራ ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ። የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸሙን እና የ2018 በጀት አመት ዕቅድን በወራቤ ከተማ ገምግሟል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ በዚሁ መድረክ ላይ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች…
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2017 በጀት አመት ከ72,400 በላይ ዜጎች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መውሰዳቸው ተገለጸ። የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2017 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸሙን እና የ2018 በጀት አመት ዕቅድን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ በተገኙበት በወራቤ ከተማ እየገመገመ ይገኛል። የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ…
በዞኑ በ2017 በጀት አመት ቴክኖሎጂ በማልማትና በመጠቀም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የጉራጌ ዞን ሳይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ገለጸ። መምሪያው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸምና በ2018 እቅድ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የጉራጌ ዞን ሳይንስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ በሰጡት ማብራሪያ በ2017 በጀት አመት ተቋማት ዲጂታላይዝድ ለማድረግ በካይዘን ፍልስፍና፣…
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ጠንካራ የቴክኖሎጂ ቁመና ለመገንባት የሚያስችሉ ስራዎች ላይ ርብርብ ይደረጋል አሉ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የክልል ቢሮዎች የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት ስራዎች ዕቅድ ግምገማ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት በርካታ ቁልፍ ተግባራትን በማከናወን የተሻለ አፈፃፀም ተመዝግቧል። በበጀት…
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ከክልል ሴክተር መስሪያ ቤት የስራ ኃላፊዎች ጋር የግብ ስምምነት ተፈራረሙ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ከክልል ሴክተር መስሪያ ቤት የስራ ኃላፊዎች ጋር የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።