
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 2ኛ ዙር ክልላዊ የሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ዐውደ_ርዕይ እና ውድድር ሰኔ 12 እና 13 በወልቂጤ ከተማ ይካሄዳል። "ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን የሳይንስ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ማዕከል እናድርግ" በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው። 2ኛውን ዙር ክልላዊ የሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ዐውደ_ርዕይ የክልሉ ትምህርት፣ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮዎች በትብብር አዘጋጅተውታል። ይህም ተማሪዎች፣ መምህራንና ኢንተርፕራይዞች ለሳይንስና ፈጠራ ስራዎች ያላቸውን ዝንባሌ ማሳደግ፣ የተሻሉ የፈጠራ ስራዎችን ማበረታታትና ዕውቅና መስጠት፣ እርስበእርስ ልምድና ተሞክሯቸውን ኢንዲለዋወጡ ማስቻ፣ የፈጠራ ስራዎቹ በማህበረሰቡ እንዲጎበኙ በማድረግና የገበያ ትስስር በመፍጠር ወደ ተግባርና አገልግሎት መቀየር ያለመ ነው። በዐውደ-ርዕዩ በተማሪዎች፣ መምህራና ኢንተርፕራይዞች የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለዕይታ ይቀርባሉ። የፌደራል፣የክልልና የዞን እንዲሁም የልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ዐውደ-ርዕዩን በመጎብኘት ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን የሳይንስ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ማዕከል ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የተለያዩ የፈጠራ ስራ ባለቤቶቾና ምሁራን በተገኙበት በፓናል ውይይት ይመክራሉ። ነጋዴዎች፣ ባለሀብቶችና የወልቂጤና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ የሳይንስ ፈጠራ ስራዎች ዐዉደ_ርዕይ እንድትጎበኙ ተጋብዛችኋል። የመጀመሪያው ዙር ክልላዊ የሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ዐውደ_ርዕይ እና ውድድር በክልሉ ትምህርት ቢሮ እና ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አዘጋጅነት በሆሳዕና ከተማ መካሄዱ ይታወሳል።