Skip to main content
zena49

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአፍሪካ ህጻናት ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ በወራቤ ከተማ በህጻናት የተዘጋጀ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ተከፈተ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሐመድ ናስር እና የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ አውደ ርዕዩን ለእይታ ክፍት አድርገዋል። "የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማነጽ ህጻናት ተኮር ተግባራትን እናከናውን" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ክልላዊ ማጠቃለያ የአፍሪካ ህጻናት ቀን በዓል በወራቤ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው በመርሐ ግብሩ በክልሉ ከተለያዩ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በተውጣጡ ህጻናት የተሰሩ ልዩ ልዩ ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎች ምልከታ እየተደረገባቸው ነው።