Skip to main content
zena50

አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመተግበርና በማስፋት ወቅቱን የሚመጥን ዲጂታል ተቋም ለመገንባት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው በዛሬው እለት በዲጂታል ሌተሪንግ ሲስተም አተገባበር ላይ በወራቤ ከተማ ለጠቅላላ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል። ‎ ‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ በክልሉ በሚገኙ ተቋማት ቴክኖሎጂን በመተግበር፣በማለማመድና በማስፋት ወቅቱን የሚመጥን ዲጂታል ተቋም ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ‎ ‎ለዚህም የሚያግዝ ተከታታይነት ያለው ስልጠና ከክልል፣ከዞን፣ከልዩ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ለተገኙ ባለሙያዎችን በተለያየ ጊዜ መሰጠቱንና ቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነ ገልጸዋል። ‎ ‎ለቢሮ ባለሙያዎች የተሰጠው ዲጂታል ሌተሪንግ ሲስተም በክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ድጋፍ በጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ እንዲሁም ከወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር የበለጸገ አዲስ ቴክኖሎጂ እንደሆነ አቶ ሰላሙ ገልጸዋል። ‎ ‎ይህም የዲጂታል ሌተሪንግ ሲስተም” በአንድ ድርጅ ውስጥ የድርጅቱን አርማ፣ ማህተም፣ የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና እንዳስፈጊነታቸው ሌሎችንም መረጃዎችን አጠቃልሎ የያዘ ወቅቱን የሚመጥን ቴክኖሎጂ መሆኑን ተናግረዋል። ‎ ‎በተለይም የአንድ ተቋም ኃላፊ ወይም ማናጀሩ በተለያየ ምክንያት ቢሮ ባይገኙ ለሥራ ጉዳይ መፈረም፣ ተቋማቸውን መምራት እንዲሁም እያንዳንዱ ደብዳቤዎችን ማባዛት እና ማስተዳደር ያስችላቸዋል ብለዋል። ‎ ‎ የቢሮው ምክትልና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ በበኩላቸው ቢሮው ቀልጣፋ፣ፈጣን እና ፍትሓዊ ተደረሽነት ያለዉ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል ውጤታማነት ላይ መሰረት ያደረጉ ስራዎችን እየሰራ ስለመሆኑን ተናግረዋል። ‎ ይ‎ህንንም ውጤታማ ለማድረ በቅርቡ ለኢኮቴ ከፍተኛ ባለሙያዎች በወራቤ ከተማ ለተከታታይ 30 ቀናት በአራት ዙር ስልጠና መሰጠቱን ገልጸው ዛሬ ለቢሮ ባለሙያዎች በዲጂታል ሌተሪንግ ሲስተም የተሰጠውን ስልጠና ወደ ሁሉም መዋቅሮች ለማስፋት የማስፋት ስራ እንደሚሰራም አብራርተዋል። ‎የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ዲጂታል ሌተሪንግ ሲስተም ብክነትን የሚያስቀር፣ ወጪንና ጊዜንና የሚቆጥብ፣ ስራን የሚያቀላጥፍ ቴክኖሎጂ እንደሆነ መገንዘብ መቻላቸውን ከስልጤ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።