Skip to main content
zena48

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለ3ኛ ዙር የሚያሰለጥናቸው የኢኮቴ ከፍተኛ ባለሙያዎችን መቀበሉን አሰወታወቀ። ‎ወራቤ-ግንቦት 16/2017-ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን ‎ቢሮው ከክልሉ ከተለያዩ መዋቅሮች ተቀብሎ በሁለት ዙር በአምስት የስልጠና ዘርፎች ሲያስተምራቸው የቆዩ 68 ባለሙያዎችን ዛሬ ያስመረቀ ሲሆን በኔትወርኪንግ፣በሳይበር ሲኩሪቲና በዳታ ቤዝ ለ3ኛ ዙር ለ7 ተከታታይ ቀናት ለማሰልጠን 34 ባለሙያዎችን ተቀብሏል። ‎ ‎የቢሮው ምክትልና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ ከክልሉ ከተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ,ዞኖች እና ልዪ ወረዳዎች የተገኙ 68 የኢኮቴ ከፍተኛ ባለሙያዎች በቆይታቸው በሁለት ዙር በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች የአድቫንስድ ቴክኒካል ስልጠና መቅሰማቸው ገልጸዋል። ‎ ‎ሰልጣኞች በስልጠናው አቅማቸውን ከማሳደግም ባለፈ በኦፍስ ማሽን ጥገናና ዕድሳት ስልጠና በተግባር ልምምድ ላይ በወራቤ ሆስፒታል፣በስልጤ ዞን ሳኢቴ መምሪያ እና በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ላይ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ 14 የቢሮ ማሽኖች ማለትም ማስተር መበዣ ማሽን 1፣ ግዙፍ ፎቶ ኮፕ ማሽን 1፣ 7 ፕርንተር፣ 5 መካካለኛ ፎቶኮፒ ማሽኖች ለተቋማት ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እንድሰጥ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ‎ ‎ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞችም እንደ ሁለተኛ ዙሮች መልካም ስነምግባር ተለብሰው የአድቫንስድ ቴክኒካል ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ራሳቸውንና ማህበረሰባቸውን ተጠቃሚ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።