Skip to main content
zena44

"የሀዲያ ዞንን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ማዕከል እናደርጋለን" - በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ 2ኛ ዙር ዞናዊ የምርምርና ፈጠራ ስራዎች ኤግዚብሽንና አውደ ርዕይ በሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ ትምህርት መምሪያ እና ሥራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ መምሪያ በጋራ የተዘጋጀ መድረክ ተካሄዷል፤ ሆሳዕና፡ ግንቦት 8/2017 ዓ.ም በአውደ ርዕዩ መክፈቻም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ም/ኃላፊና የሳይንስ ፈጠራ ስራዎች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙዲን ሀሰን፣ የሀዲያ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ፣ የዞን አስተባባሪዎች፣ የየመመሪያው የስራ ኃላፊዎች፣ የፈጠራ ባለቤቶችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። በኤግዚቢሽኑም የፈጠራ ስራዎች አውደ ርዕይ ተመርቆ በመከፈት ጉብኝት ተርጎባቸዋል። የሀዲያ ዞን ም/አስተዳዳሪና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር በፍቃዱ ገ/ሃና መንግስት ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች መካከል የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች አንዱ ከመሆኑ አንጻር የተማሪዎች የፈጠራ ስራዎች የሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግር ለመፍታት ሚናቸው የጎላ ነውና የፈጠራ ስራዎች በዞኑ አስተዳደርና በባለድርሻ ተቋማት እየተደገፈና እየተበረታታ ይገኛል ብለዋል። በዚህ የፈጠራ ስራ የፈጠራ ባለቤት ተማሪዎች ከትምህርት ቤቶች አንስቶ እሰከ ሀገር አቀፍ ደረጃ በሚደረጉ የፈጠራ ስራ ውድድሮች የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሪት ገነት ሙልጌታ በተማሪዎች የሚሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ከፈርጀ ብዙ ችግር ፈቺነት አንጻር የፈጠራ ስራዎችን ማበረታታትና የማስተዋወቅ ስራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ጂጅታል ቴክኖሎጂ እያደረገች ላለው ለውጥና ግስጋሴ የፈጠራ ስራዎችንና የፈጠራ ባለቤቶችን ማበረታታትና መደገፍ የመምሪያው ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የገለጹት ወይዘሪት ገነት ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንዳለም ጠቁመዋል። የሀዲያ ዞን የስራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሊረንሶ በበኩላቸው የፈጠራ ስራ ለአጠቃላይ የህብረተሰብ እድገት የሚጫወተው ሚና የላቀ ነው ብለዋል። የፈጠራ ስራ ለወጣቶች አንዱ የስራ ዕድል የሚፈጠርበት መስክ በመሆኑ መምሪያው ለዚህ ተግባር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በመድረኩ ማጠቃለያም ለፈጠራ ስራዎችና ለፈጠራ ባለቤቶች የማበረታቻና የዕውቅና መርሀግብር ተካሄዷል።/p>