
ክልሉ በቱሪዝም ዘርፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ለማስተዋወቅ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዌብሳይት ፋይዳው የጎላ እንደሚሆን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ ክልሉ በቱሪዝም ዘርፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ለማስተዋወቅ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዌብሳይት ፋይዳው የጎላ እንደሚሆን ገልፀዋል። ኃላፊው እንደገለፁት ከክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በቅንጅት የበለፀገው ዌብሳይት ርክክብና የቱሪዝም ማኔጅመንት ሲስተም ላይ የምክክር መድረክ ባካሄዱበት ወቅት ነው። እንደሀገር የብዝሃ ኢኮኖሚ ዘርፍ አንዱ የቱሪዝም ዘርፍ በመሆን በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝ ገልፀዋል። ዌብሳይት ቴክኖሎጂው በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም ዘርፍ እንቅስቃሴ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ በዘርፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ለማስተዋወቅ ዕድል እንደሚፈጥር ያስችላል ብለዋል። የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለዘርፍ ትኩረት በመስጠት የዲጂታል ቴክኖሎጂን በማበልጸግ ርክክብ በመደረጉ አመስግነዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ በበኩላቸው የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ለማስተዋወቅና ለመሸጥ ጥራት ያለው ዌብሳይት በራስ አቅም ማልማት መቻሉን ተናግረዋል። ዲጂታል ቴክኖሎጂ ክልሉ ለማስተሳሰር የሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ጥረቶች በማድረግ ስራዎች በመስራት እንደሚገኝ የገለፁት ኃላፊው በቀጣይ የበለፀገዉ ዌብሳይት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደስራ ማስገባት እንደሚገባ አንስተዋል። ቴክኖሎጂዎች በየትኛውም ቦታ ሆኖ መረጃዎችን የማግኘትና የመቆጣጠር አቅም ከፍተኛ በመሆኑ በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝ ጠቅሰው የቱሪዝም ማኔጅመንት ሲስተም አጋዥ እንደሚሆን አብራርተዋል። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ብሩክታይት ፀጋዬ ምስራቅ ዞኑ የቱሪስት መስብ መዳረሻዎች መሆኑን ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ተናግረዋል። በዞኑ ማህበረሰብ በርካታ የባህላዊ ዳኝነት ስርዓቶች ባለቤት በመሆኑ አንስተዋል። በዕለቱ በዌብሳይትና የቱሪዝም ማኔጅመንት ሲስተም ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ማብራሪያ ቀርቦ ምክክር ተደርጎባቸዋል። በመድረኩ የክልሉ ባህል ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ የክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂና ቢሮ ሃላፊ ሰላሙ አማዶ ፣የክልሉ ባህል ቱሪዝም ምክትልና የቱሪዝም ዘርፍ ሃላፊ አቶ ኑሪ ከድር ፤ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።