Skip to main content
zena42

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከክልልሉ ከሁሉም ዞኖች፤ ልዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት ለተውጣቱ የኢኮቴ ከፍተኛ ባለሙያዎች በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች የአድቫንስድ ቴክኒካል ስልጠና መስጠት ጀመረ።  ‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ፤ በቢሮ ማሽን ጥገናና ዕድሳት፣ በኔትወርክ ልማትና አስተዳደር እና በሶፍትዌር ልማት ማበልጸግ ዙሪያ በወራቤ ከተማ መስጠት በጀመረው ስልጠና ላይ የሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ የዞኖች፣ የልዩ ወረዳዎች እና የከተማ አስተዳደሮች የኢኮቴ ከፍተኛ ባለሙያዎች እተሳተፉበት ይገኛል። ‎ ‎የስልጠና መርሃ ግብሩን በይፋ ያስጀመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ ባስተላለፉት መልዕክት ቴክኖሎጂን ማልማትና መጠቀም እንዲሁም በዲጂታል ስርዓት እንዲመሩ ማድረግ አለም የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ለመድረስ ብሎም በሀገር ደረጃ የታለመውን ሁሉን አቀፍ ብልጽግና ከግብ ከማድረስ አንጻር ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡ ‎እንደ ሀገር ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን እናድርግ በሚል ግብ ተጥሎ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ያሉት የቢሮው ሀላፊ ዲጅታል ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን ለማረጋገጥም የዘርፉ ባለሙያዎችን በዲጅታል እውቀትና ክህሎት ማስታጠቅ ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር ነው ብለዋል። ‎ ‎ዲጅታል ክህሎትን ለማስጨበጥ በተለያየ መልኩ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን የገለጹት አቶ ሰላሙ ይህን ስልጠና ልዩ የሚያደርገው በትላልቅ ካምፓኒዎች ደረጃ የሚሰጥ አድቫንስድ ቴክኒካል ስልጠና መሆኑ ነው ብለዋል። ‎ ‎ይህ ስልጠና ሰልጣኞች አሁን ላይ ለሚያከናውኑት ተግባር ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩም የህይወት ምእራፋቸው ወሳኝ በመሆኑ በአራት ዙር ለአንድ መቶ አስራ ሁለት ሰልጣኞች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚሰጠውን ስልጠና ሰልጣኞች በአግባቡ ተከታትለው በቂ እውቀትና ክህሎት ጨብጠው የማህበረሰባችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን እንዲያከናውኑና ራሳቸውን ሊለውጡበት እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል። ‎ ‎ የቢሮው ምክትልና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ በበኩላቸው የስልጠናውን አላማ በማብራራት ሰልጣኞች በቆይታቸ ሊላበሱት የምገባ የስነምግባር መመሪያ አስገንዝበዋል። ‎ ‎በስልጠናው መክፈቻ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶን ጨምሮ ከክልሉ ከተለያዩ መዋቅሮች የተገኙ የኢኮቴ ከፍተኛ ባለሙያዎችና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ማኔጅመንት አካላት ተገኝተዋል፡፡