Skip to main content
zena84

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ ከክልሉ ሳይንስ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር ያስለማዉን የተቋሙን ዌብ ሳይት ተረክቧል፡፡ በርክክቡ ወቅት የቢሮዉ ሃላፊ የተከበሩ አቶ ገብሬ ጋጌ ባስተላለፉት መልዕክት ዌብ ሳይቱን በማልማት ላቀረበዉ የክልሉ ሳይንስ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምስጋናቸዉን አቅርበዉ ዌብ ሳይቱ በክልሉ በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችን ለዓለም በማጋራት ከዓለማቀፉ ማህበረሰብ ጋር ተቋሙን የምናገናኝበት፣ለተቋሙ ተገልጋዮች ወቅታዊ መረጃዎችን የምንሰጥበት እንዲሁም የምንሰጣቸዉን አገልግሎቶች፣አገልግሎቶቹን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችንና አገልግሎቱን ለማግኘት የሚወስደዉን ሰዓት በግልፅ በማሳወቅ አፈፃፀማችንን ለማላቅ ከተገልጋዮቻችን አስተያየቶችን ኦንላየን የምንቀበልበትን እድል እንደሚፈጥር አስገንዝበዋል፡፡ በመሆኑም ይህንን ዘመኑ የደረሰበትን ቴክሎሎጂ በመጠቀም የለማ ዌብ ሳይት እንደተቋም በማስተዋወቅ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ማስተዳደር እንደሚገባና ወቅታዊ መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የስራ መመሪያ ተሰጥቶ የርክክብ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡ የቢሮዉ ዌብ ሳይት አድራሻ ፡- www.cepsb.gov.et