ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ። ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል። የመግባቢያ ሰነድ የመፈራረም ዓላማ በዋናነት በክልሉ ለሚገኘው ማህበረሰብ ያለውን ችግር መነሻ ያደረገ የቴክኖሎጂ መፍትሔ መፈለግ እና አብሮ መስራትን መጠናከር እንደሆነ ተገልጿል። የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት እንደገለፁት፥ የጥናቱ ሂደት የተፋጠነ እንዲሆን ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ይደረጋል ብለዋል። አክለውም ፕሬዝዳንቱ ዩኒቨርሲቲው በክልሉ ከዚህ በፊት በከበረ ድንጋይ ዙሪያ ያደረገውን የጥናት ውጤት ተሰንዶ እንዲቀመጥ አቅጣጫ ሰጥተዋል። በዚህ የጥናት ውጤት መነሻ ያደረገው በግብርና የስንዴ ምርትና ምርታማነት መጨመር ላይ እና በማዕድን ዘርፍ የከበረ ድንጋይ ሲሆን፤ ዓላማው በክልሉ ያለውን ፀጋ ለመጠቀም የሚያስችል የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግ እንደሆነ አብራርተዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ በበኩላቸው፥ የመጭውን ትውልድ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተቋማት ተቀራርቦና ተቀናጅቶ መስራትና የተሻለ ወውጤት ለመምጣት መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል። በመጨረሻም ጥናቱ በስድስት ወር እንደሚጠነቀቅ ያነሱት ኃላፊው፤ ጥናቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠነቀቅ ጠንካራ ድጋፍ እንደሚደረግ ጠቅሰዋል።