Skip to main content
zena62

የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ አስመልክቶ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። ወራቤ፣ መስከረም 8/2018 (ስልጤ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን) ከስልጤ ዞን የተለያዩ አከባቢዎች የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበትና በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ምረቃ በማስመልከት የተዘጋጀ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። ህዝባዊ ሰልፉ ኢትዮጵያዊያን ከትልቅ እስከ ትንሽ ሀብታም ደሃ ሳይሉ አሻራቸውን ላሳረፉበት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት የደስታ መግለጫና በቀጣይ ጊዜያት መንግስት ለሚያከናውናቸው ዋና ዋና የልማት እንቅስቃሴዎች አጋርነት ለማሳየት ያለመ መሆኑ ተገልጿል። ታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ በህብረት ችለናል በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ:- ‎*በህብረት ችለናል! ‎* የሕዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ምልክት! ‎*ከጨለማ ወደ ብርሃን! ‎* የሕዳሴ ግድብ የብልጽግናችን አሻራ! ‎*ግድባችን! የመቻል ማሳያ የማንሰራራት ጅማሮ ምልክት! ‎ ‎*የሚደገም ድል፣ የሚጨበጥ ብስራት - ሕዳሴ ግድብ! ‎ ለግድቡ የተባበረ ክንድ ለብልጽግናችን ይተጋል! ‎ ‎*ግድባችን በራስ አቅም በአፍሪካዊነት ኩራት የተገነባ እውነት! እና ሌሎች የተለያዩ መልዕክቶች እየተላለፉበት ይገኛል። ‎ በህዝባዊ ሰልፉ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማሕበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ሀላፊና የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ክብርት ወ/ሮ ነዒማ ሙኒር፣ የስልጤ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት መህዲያ ቡሴር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማህበራዊ ክላስተር አመራሮች፣ የስልጤ ዞን አመራር አካላትና ከሁሉም መዋቅሮች የመጡ የማህበረሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።